Added: 2 years ago
ቀደም ሲል ስልጠናን እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን ያለልዩነት ለሁሉም አርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ በጀምላ ይከናወኑ እንደነበር ይታወሳል። ይህ አይነት የተለመደ አሰራር የስልጠና ፍላጎትን ከተሳታፊ አርሶአደሮች ክፍተት ለይቶ ለመፍታት በማለም መነሻ ያላደረገ እንደመሆኑ በስራቸው ላይ ሊያስገኝ የሚችለው ውጤትም ሆነ ያለውን የአቅም ችግር በመፍታት በኩል ውስንነት ያለበት ይሆናል። ስልጠና ለመስጠት የሚታዩ ክፍተቶችን እና ችግርን በለየ ፍላጎትን መሰረት አድርጎ ካልተሰጠ በተቋሙ ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። በመሆኑም ክፍተትን ለይቶ ለመሙላት ባለመ መንገድ የስልጠና ቁሳቁሶችን ቀድሞ በማዘጋጀት ስልጠናውን የተሟላ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።